ኤልያስም ሕዝቡን አለ፥ “ከእግዚአብሔር ነቢያት አንድ እኔ ብቻ ቀርቻለሁ፤ የበዓል ነቢያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማምለኪያ ዐፀድ ነቢያትም አራት መቶ ናቸው።
1 ነገሥት 18:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ወይፈኖች ይሰጡን፤ እነርሱም አንድ ወይፈን ይምረጡ፤ እየብልቱም ይቍረጡት፤ በእንጨትም ላይ ያኑሩት፤ በበታቹም እሳት አይጨምሩ፤ እኔም ሁለተኛውን ወይፈን አዘጋጃለሁ፤ በእንጨቱም ላይ አኖረዋለሁ፤ በበታቹም እሳት አልጨምርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት ወይፈኖች ስጡን፤ እነርሱም አንዱን መርጠው ይውሰዱ፤ በየብልቱም ቈራርጠው፣ በዕንጨት ላይ ያኑሩት፤ ግን እሳት አያንድዱበት፤ እኔም ሁለተኛውን ወይፈን አዘጋጃለሁ፤ በዕንጨትም ላይ አኖረዋለሁ፤ እሳት አላነድድበትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ሁለት ኰርማዎችን አምጡና የባዓል ነቢያት አንዱን ወስደው ይረዱት፤ ሥጋውንም ቆራርጠው እንጨት በመረብረብ በዚያ ላይ ያኑሩት፤ ነገር ግን በእሳት አያቀጣጥሉት፤ እኔም ሁለተኛውን ኰርማ ወስጄ እንደዚሁ አደርጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ሁለት ኰርማዎችን አምጡና የባዓል ነቢያት አንዱን ወስደው ይረዱት፤ ሥጋውንም ቈራርጠው እንጨት በመረብረብ በዚያ ላይ ያኑሩት፤ ነገር ግን በእሳት አያቀጣጥሉት፤ እኔም ሁለተኛውን ኰርማ ወስጄ እንደዚሁ አደርጋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ወይፈኖች ይሰጡን፤ እነርሱም አንድ ወይፈን ይምረጡ፤ በየብልቱም ይቁረጡት፤ በእንጨትም ላይ ያኑሩት፤ በበታቹም እሳት አይጨምሩ፤ እኔም ሁለተኛውን ወይፈን አዘጋጃለሁ፤ በእንጨቱም ላይ አኖረዋለሁ፤ በበታቹም እሳት አልጨምርም። |
ኤልያስም ሕዝቡን አለ፥ “ከእግዚአብሔር ነቢያት አንድ እኔ ብቻ ቀርቻለሁ፤ የበዓል ነቢያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማምለኪያ ዐፀድ ነቢያትም አራት መቶ ናቸው።
እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈጣሪዬን የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መልካም ነው” ብለው መለሱ።
የአሮንም ልጆች ካህናቱ የተቈረጡትን ብልቶች፥ ራሱንም፥ ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ይረበርቡታል።