አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በዘመናቸው ሁሉ ሲዋጉ ኖሩ።
አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ዘመነ መንግሥታቸውን ያሳለፉት፣ እርስ በርስ በመዋጋት ነበር።
የይሁዳ ንጉሥ አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባዕሻ በሥልጣን በነበሩበት ዘመን ሁሉ በማያቋርጥ የእርስበርስ ጦርነት ላይ ነበሩ።
በአሳና በእስራኤል ንጉሥ በባኦስ መካከል በዘመናቸው ሁሉ ሰልፍ ነበረ።
በዘመኑም ሁሉ በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበረ።
በአሳና በእስራኤል ንጉሥ በባኦስ መካከል በዘመናቸው ሁሉ ጦርነት ነበረ።
አሳም በነገሠበት ዘመን እስከ ሠላሳ አምስተኛው ዓመት ድረስ ጦርነት አልነበረም።