እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
1 ዮሐንስ 5:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምንለምነውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ የለመንነውንም ነገር እንደ ተቀበልን እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምንጠይቀውን እንደሚሰማን ካወቅን፥ የጠየቅነውን እንደ ተቀበልን እናውቃለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምንለምነውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን ከእርሱ የምንለምነውን ሁሉ አሁኑኑ እንደምንቀበል እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። |
እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
እግዚአብሔር ከኃጥኣን ፈጽሞ ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። ከዐመፃ ጋር ካለ ብዙ ሀብት ይልቅ፥ ከእውነት ጋር ያለ ጥቂት ሀብት ይሻላል። አካሄዱ ከእግዚአብሔር ይቃናለት ዘንድ፥ የደግ ሰው ልብ እውነትን ያስባል።