La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዮሐንስ 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእርሱ የሚኖር ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፤ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በርሱም የሚኖር ኀጢአትን አያደርግም፤ ኀጢአት የሚያደርግ ግን እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእርሱ የሚኖር ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፤ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም፥ አላወቀውምም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ በክርስቶስ የሚኖር ሰው ሁሉ ኃጢአት አይሠራም። ኃጢአት የሚሠራም ሰው ክርስቶስን አላየውም ወይም አላወቀውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእርሱ የሚኖር ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፤ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም።

Ver Capítulo



1 ዮሐንስ 3:6
11 Referencias Cruzadas  

እኛስ ሁላ​ችን ፊታ​ች​ንን ገል​ጠን በመ​ስ​ተ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እና​ያ​ለን፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ እንደ ተሰ​ጠን መጠን የእ​ር​ሱን አር​አያ እን​መ​ስል ዘንድ ከክ​ብር ወደ ክብር እን​ገ​ባ​ለን።


በጨ​ለማ ውስጥ “ብር​ሃን ይብራ” ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፊት የክ​ብ​ሩን ዕው​ቀት ብር​ሃን በል​ባ​ችን አብ​ር​ቶ​ል​ና​ልና።


አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።


ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።


አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።


ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።


ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።


ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።


ወዳጅ ሆይ! በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።