ዳግመኛም በሦስተኛው ቀን ውኃውን ከምድር በሰባተኛው እጅ ላይ እንዲሰበሰብ አዘዝኸው። የምድር ስድስቱ እጅም በውስጣቸው ያርሱ ዘንድ፥ ዘርም ይዘሩ ዘንድ፥ በፊትህም ይኖሩ ዘንድ ደረቅ ሆኖ ይቅር አልህ።