እንዲህም አልሁት፥ “አቤቱ የፈጠርሃቸውን በአንድ ጊዜ በአንድነት እንደምታስነሣቸው ለእኔ ለባሪያህ እንዴት ነገርኸኝ? የፈጠርሃቸውንም በአንድ ጊዜ ፈጥነህ የምታስነሣቸው ከሆነ ዓለም ይጨነቃል፤ ይህም ባይሆን ዛሬ ካሉት ጋራ አንድ ጊዜ ሊሸከማቸው በቻለ ነበር።”