እርሱም መለሰልኝ እንዲህም አለኝ፥ “ዘጠኝ ወር ከተፈጸመ በኋላ በማኅፀንዋ ያለውን ልጅዋን ማስቀረት ይቻላት እንደ ሆነ ሄደህ የፀነሰች ሴትን ጠይቃት።”