እኔ ግን የልዑልን መንገድ እጠይቅ ዘንድ አልወደድሁም፤ ሁልጊዜ በእኛ ላይ ስለሚያልፈው እንጂ፤ እስራኤል በውርደት ለአሕዛብ፥ የወደድኸውም ሕዝብ ለኀጢአተኞች ሕዝብ ተሰጥቶአልና። የአባቶቻችንም ኦሪት ጠፍታለችና፤ በውስጧም የተጻፈው ቃል ኪዳን የለምና።