እርሱንም የጽድቅ ትእዛዝን አዘዝኸው፤ ትእዛዝህንም አፈረሰ፤ ከዚህም በኋላ በእርሱና በልጆቹ ላይ ሞትን አመጣህ፤ አሕዛብና ሕዝብ፥ ነገድና ቍጥር የሌላቸው መንደረተኞችም ከእርሱ ተወለዱ።