ከተማችን ኢየሩሳሌም በጠፋች በሠላሳ ዓመት ዕዝራ የተባልሁ እኔ ሱቱኤል በባቢሎን ነበርሁ፤ በመኝታዬም ደንግጬ ነበርሁ፤ ፊቴም ተገልጦ ነበር። በልቡናዬም ዐሳቤ ይወጣና ይወርድ ነበር።