1 ቆሮንቶስ 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያደርሰንም፤ ብንበላም አይረባንም፤ ባንበላም አይጎዳንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ምግብ ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላ የሚጐድልብን ነገር የለም፤ ብንበላም የምናተርፈው ነገር አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም አይተርፈንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳሩ ግን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን መብል አይደለም፤ ባንበላም የሚጐድልብን ነገር የለም፤ ብንበላም የምናተርፈው ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም አይተርፈንም። |
መብል ለሆድ ነው ፤ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ይሽራቸዋል፤ ሥጋችሁም ለእግዚአብሔር ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ እግዚአብሔርም ለሥጋችሁ ነው።
ሌላ ልዩ ትምህርት አታምጡ፤ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።