1 ቆሮንቶስ 7:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብታገባም ኀጢአት አይሆንብህም፤ ድንግሊቱም ባል ብታገባ ኀጢአት አይሆንባትም፤ ያገቡ ግን ለራሳቸው ድካምን ይሻሉ፤ እኔም ይህን የምላችሁ ስለማዝንላችሁ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብታገባ ግን ኀጢአት አልሠራህም፤ ድንግሊቱም ብታገባ ኀጢአት አላደረገችም። ነገር ግን የሚያገቡ ሰዎች በዚህ ዓለም ብዙ ችግር ይገጥማቸዋል፤ እኔም ይህ እንዳይደርስባችሁ እወድዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም፤ ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይገጥማቸዋል፤ እኔም ከዚያ ባስጣልኳችሁ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አንተ ሚስት ብታገባ ኃጢአት ይሆንብሃል ማለት አይደለም፤ እንዲሁም አንዲት ልጃገረድ ባል ብታገባ ኃጢአት ይሆንባታል ማለት አይደለም፤ ይሁን እንጂ የሚያገቡ ሰዎች በዚህ ዓለም ብዙ የኑሮ ችግር ይገጥማቸዋል፤ የእኔም ምኞት ከዚህ ችግር እንድትድኑ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይሆንባቸዋል፥ እኔም እራራላችሁ ነበር። |
ነገር ግን ወንድሞቻችን እንዲህ ይቀናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያልፍ ቀርቦአልና፤ አሁንም ያገቡ እንዳላገቡ ይሆናሉ።
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።