1 ቆሮንቶስ 7:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም የማያምንና ሚስቱንም የሚያፈቅር ከእርስዋም ጋር ሊኖር የሚወድ ባል ቢኖራት ባልዋን አትፍታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያላመነ ባል ያላት ሴት ብትኖርና እርሱም ዐብሯት ለመኖር የሚፈቅድ ከሆነ፣ ልትፈታው አይገባትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርሷ ጋር ለመኖር ቢስማማ፥ አትተወው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክርስቲያን ሴት ክርስቲያን ያልሆነ ባል ቢኖራትና አብሮአት ለመኖር ቢፈልግ አትፍታው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርስዋ ጋር ሊቀመጥ ቢስማማ፥ አትተወው። |
ሌላውን ግን ከራሴ እናገራለሁ፤ ከጌታችንም አይደለም፤ ከወንድሞቻችን መካከል የማታምን፥ ባልዋንም የምታፈቅር ከእርሱም ጋር ለመኖር የምትወድ ሚስት ያለችው ሰው ቢኖር ሚስቱን አይፍታ።
የማያምን ባል በሚስቱ ይቀደሳልና፤ የማታምን ሚስትም በባልዋ ትቀደሳለችና፤ ያለዚያማ ልጆቻቸው ርኩሳን ይሆናሉ፤ አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው።