1 ቆሮንቶስ 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያገቡትንም በእግዚአብሔር ትእዛዝ አዝዛቸዋለሁ፤ በራሴ ትእዛዝም አይደለም፤ ሚስትም ከባልዋ አትፋታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላገቡት ይህን ትእዛዝ እሰጣለሁ፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ እንጂ የእኔ አይደለም። ሚስት ከባሏ አትለያይ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላገቡት ግን የምሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤ ያገባች ሴት ከባሏ አትለይ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላገቡት ግን የምሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤ ያገባች ሴት ከባልዋ አትለይ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥ ባልም ሚስቱን አይተዋት ብዬ የተጋቡትን አዛቸዋለሁ፥ እኔ ግን አላዝም፥ ጌታ እንጂ። |
ሌላውን ግን ከራሴ እናገራለሁ፤ ከጌታችንም አይደለም፤ ከወንድሞቻችን መካከል የማታምን፥ ባልዋንም የምታፈቅር ከእርሱም ጋር ለመኖር የምትወድ ሚስት ያለችው ሰው ቢኖር ሚስቱን አይፍታ።
ስለ ደናግልም የምነግራችሁ የእግዚአብሔር ትእዛዝ አይደለም፤ ታማኝ እንድሆን እግዚአብሔር ይቅር ያለኝ እንደ መሆኔ ምክሬን እነግራችኋለሁ እንጂ።