1 ቆሮንቶስ 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቋንቋ የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ የሚተረጕም ግን የክርስቲያን ማኅበርን ያንጻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ያንጻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ያንጻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ሰው ራሱን ብቻ ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበረ ክርስቲያንን ያንጻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል። |
ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥ ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል።
እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሾማቸው አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም መምህራንን፥ ከዚህም በኋላ ተአምራትና ኀይል ማድረግ የተሰጣቸውን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመርዳትም ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመምራትና ቋንቋን የመናገር ሀብት የተሰጣቸውን ነው።
የሰውን ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ የመላእክትንም ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌለኝ እንደሚጮህ ነሐስ፥ ወይም እንደሚመታ ከበሮ መሆኔ ነው።
ትንቢት ብናገር፥ የተሰውረውን ሁሉ፥ ጥበብንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍለስ የሚያደርስ ፍጹም እምነትም ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
አሁንም ቋንቋ መናገር ለማያምኑ ሰዎች ለምልክት ነው፤ ለሚያምኑ ግን አይደለም፤ ትንቢትም ለሚያምኑ ነው እንጂ ለማያምኑ አይደለም።
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ሁላችሁ በምትሰበሰቡበት ጊዜ መዝሙር አላችሁ፤ ትምህርት አላችሁ፤ መግለጥ አላችሁ፤ በቋንቋ መናገር አላችሁ፤ መተርጐምም አላችሁ፤ ሁሉም ለሚታነጽበት ጥቅም አድርጉት።
ሁላችሁም በቋንቋ ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ይልቁንም ትንቢት ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ሳይተረጕም በቋንቋ ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር እጅግ ይበልጣልና፤ ቢተረጕም ግን ማኅበሩን ያንጻል።