ጌታም አንድ ሲሆን ልዩ ልዩ አገልግሎቶች አሉ።
አገልግሎትም ልዩ ልዩ ሲሆን፣ ጌታ ግን አንድ ነው፤
ጌታም አንድ ሲሆን፤ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችም አሉ፤
ልዩ ልዩ አገልግሎቶች አሉ፤ ጌታ ግን አንድ ነው።
አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤
ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና ‘ሊቃውንት’ ተብላችሁ አትጠሩ።
ቃሉን ለእስራኤል ልጆች ላከ፤ በኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምን ነገራቸው፤ እርሱም የሁሉ ገዢ ነው።
መንፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆን ስጦታው ልዩ ልዩ ነው።
ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔርም አንድ ሲሆን ልዩ ልዩ አሠራር አለ።
ለእኛስ ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ እኛም በእርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አለን።
አንደበትም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ክብር ጌታ እንደ ሆነ ያምን ዘንድ ነው።