እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።”
1 ቆሮንቶስ 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረም፤ ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ሴት ለወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴት ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሴት ለወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረምና። |
እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።”
አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው። ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።