1 ቆሮንቶስ 11:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሰብሰባችሁ ለፍዳ እንዳይሆን፥ የተራበ ቢኖር በቤቱ ይብላ፤ አትነቃቀፉም፤ ሌላውን ሥርዐት ግን መጥቼ እሠራላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለፍርድ እንዳይሆንባችሁ፣ ማንም የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር ደግሞ በምመጣበት ጊዜ እደነግጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም የራበው ቢኖር፥ ለፍርድ እንዳትሰበሰቡ፥ በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር በመጣሁ ጊዜ መመሪያ እሰጣችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሰብሰባችሁ ለፍርድ እንዳይሆን ከመካከላችሁ የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር እኔ እዚያ ስመጣ ተጨማሪ መመሪያ እሰጣችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም የራበው ቢኖር ለፍርድ እንዳትሰበሰቡ በቤቱ ይብላ። የቀረውንም ነገር በመጣሁ ጊዜ እደነግጋለሁ። |
እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያንጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ ሰው ሁሉ በየሳምንቱ እሑድ የተቻለውን ያወጣጣ፤ ያገኘውንም በቤቱ ይጠብቅ።
ስለዚህም በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዳስተማርሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የሄድሁበትን መንገድ ይገልጥላችሁ ዘንድ በእግዚአብሔር የታመነና ልጄ ወዳጄ የሆነ ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ።
እንኪያስ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ፈጥኜ እመጣለሁ፤ ነገር ግን የትዕቢተኞችን ነገር አልሻም፤ ኀይላቸውን እሻለሁ እንጂ።
ነገር ግን ሁሉ እግዚአብሔር እንደ አደለው፥ ሁሉም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ እንዲህ ሥርዐት እንሠራለን።