በሥጋዊ ሕግም ትኖራላችሁና እርስ በርሳችሁ የምትቃኑና የምትከራከሩ ከሆነ ግን ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? እንደ ሰው ልማድስ የምትኖሩ መሆናችሁ አይደለምን?
1 ቆሮንቶስ 11:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሁሉ አስቀድሞ በቤተ ክርስቲያን በምትሰበሰቡ ጊዜ እንደምትጣሉና እንደምትከራከሩ ሰምቻለሁ፤ የማምነውም አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሁሉ አስቀድሞ በቤተ ክርስቲያን በምትሰበሰቡበት ጊዜ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ ሰምቻለሁ፤ ይህም ሊሆን እንደሚችል በከፊል አምናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጀመሪያ እንደ ማኅበር ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ እሰማለሁና፤ በከፊል ያን አምናለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሁሉ በፊት በማኅበር በምትሰበሰቡበት ጊዜ በመካከላችሁ መለያየት መኖሩን ሰምቼአለሁ፤ የሰማሁትም ነገር በከፊል እውነት መሆኑን አምናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያ ወደ ማኅበር ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ እሰማለሁና፥ በአንድ በኩልም አምናለሁ። |
በሥጋዊ ሕግም ትኖራላችሁና እርስ በርሳችሁ የምትቃኑና የምትከራከሩ ከሆነ ግን ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? እንደ ሰው ልማድስ የምትኖሩ መሆናችሁ አይደለምን?
በእናንተ ላይ ዝሙት ይሰማል፤ እንደዚህ ያለው ዝሙትም አረማውያን እንኳ የማያደርጉት ነው፤ ያባቱን ሚስት ያገባ አለና።
እንግዲህ በሚነቅፉ ሰዎች ዘንድ ልትከራከሩ አትድፈሩ፤ ከጓደኛው ጋር በዐመፀኞች ዘንድ ሊከራከር የሚችል አለን? በደጋጎች ዘንድ አይደለምን? ከባልንጀራው ጋር ክርክር ያለው ቢኖርም በቅዱሳን ዘንድ ይከራከር፤ በሚነቅፉና በዐመፀኞች ዘንድ ግን አይደለም።