ቀድሞ በመጀመሪያ ዘመን ጠጕሩ ይከብደው ነበርና በዓመት አንድ ጊዜ ይቈረጠው ነበር፤ ሲቈረጥም የራሱ ጠጕር በንጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ያህል ይመዝን ነበር።
1 ቆሮንቶስ 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተፈጥሮዋስ አያስረዳችሁምን? ወንድ ግን ጠጕሩን ቢያሳድግ ነውር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድ ጠጕሩን ቢያስረዝም ነውር እንደሚሆንበት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድ ጠጒሩን ቢያስረዝም ነውር እንደሚሆንበት ተፈጥሮ ራሱ ያስተምራችሁ የለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት፥ ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታልና። |
ቀድሞ በመጀመሪያ ዘመን ጠጕሩ ይከብደው ነበርና በዓመት አንድ ጊዜ ይቈረጠው ነበር፤ ሲቈረጥም የራሱ ጠጕር በንጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ያህል ይመዝን ነበር።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ አባቴን አከብራለሁ እንጂ ጋኔን የለብኝም፤ እናንተ ግን ትንቁኛላችሁ።