ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ በኬርዩ፥ እስማኤል፥ ሰዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ ሁሉ የአሴል ልጆች ነበሩ።
1 ዜና መዋዕል 8:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድሙም የአሴል ልጆች፤ በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኤያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንድሙ የኤሴቅ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛ ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛ ልጁ ኤሊፋላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድሙም የአሴል ልጆች፤ በኩሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአጼል ወንድም ዔሼቅም በኲሩ ኡላም፥ ሁለተኛው ያዑሽና ሦስተኛ ኤሊፌሌጥ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድሙም የአሴል ልጆች፥ በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት። |
ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ በኬርዩ፥ እስማኤል፥ ሰዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ ሁሉ የአሴል ልጆች ነበሩ።
የኡላም ልጆች ጽኑዓን ኀያላንና ቀስተኞች ነበሩ፤ ለእነርሱም መቶ አምሳ የሚያህሉ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ልጆች ነበሩ።