ኢያሱብን፥ ሻክያን፥ ሜርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ።
ይዑጽን፣ ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤ እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው።
ይዑጽን፥ ሻክያን፥ ሚርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ።
የዑጽ፥ ሳክያና ሚርማ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ የእርሱ ወንዶች ልጆች በሙሉ የቤተሰብ አለቆች ሆኑ።
ይዑጽን፥ ሻክያንና ሚርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ።
ከሑሲምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ።
ከሚስቱ ከሖዲሽ ዮባብን፥ ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፤