እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
1 ዜና መዋዕል 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ጋር በየትውልዳቸው በየአባቶቻቸው ቤት ለሰልፍ የተዘጋጁ የሠራዊት ጭፍሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶችና ልጆች ነበሩአቸውና ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሯቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺሕ ሰዎች ነበሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም ጋር በየትውልዳቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ለውግያ የተዘጋጁ የሠራዊት ጭፍሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶችና ልጆች ነበሩአቸውና ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ብዙ ሚስቶችና ብዙ ልጆች ስለ ነበሩአቸው ዘሮቻቸው ለወታደራዊ አገልግሎት የደረሱ ሠላሳ ስድስት ሺህ ወንዶች ማቅረብ ይችሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ጋር በየትውልዳቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ለሰልፍ የተዘጋጁ የሠራዊት ጭፍሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶችና ልጆች ነበሩአቸውና ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ። |
እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
ወንድሞቻቸውም በይሳኮር ወገኖች ሁሉ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች በትውልዳቸው ሁሉ የተቈጠሩ ሰማንያ ሰባት ሺህ ነበሩ።