1 ዜና መዋዕል 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጋድም ልጆች በባሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ በአፋዛዣቸው ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋድ ነገድ ደግሞ ከእነርሱ ቀጥሎ እስከ ሰልካ ድረስ በሚገኘው በባሳን ምድር ኖሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጋድም ልጆች ከሮቤል ነገድ አጠገብ ባለው በባሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጋድ ነገድ፥ የሮቤል ነገድ ከሚኖሩበት በስተ ሰሜን ባለው ምድር ይኖሩ ነበር፤ ይህም ምድር በባሳን ውስጥ ሲሆን በስተ ምሥራቅ እስከ ሳለካ ይደርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋድም ልጆች በባሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ በፊት ለፊታቸው ተቀመጡ። |
የአርሞንኤምን ተራራ፥ ካሴኪን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌርጌሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ፤
ገለዓድንም፥ የጌሴሪያውያንንና የመከጢያውያንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳንንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥