ንጉሡም ዳዊት ኦርናን፥ “አይደለም፥ ነገር ግን ለአንተ ያለውን ለእግዚአብሔር አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት በከንቱ አላቀርብምና በተገቢው ዋጋ እገዛዋለሁ” አለው።
1 ዜና መዋዕል 4:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤዜራስም ልጆች፤ ኢያቴር፥ ሞራድ፥ ጋፌር፥ ኢያሎን ነበሩ፤ ኢያቴርም ማሮንን፥ ሰማዒን፥ የኢስቲሞንን አባት ይስባኤልን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዕዝራ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ሜሬድ፣ ዔፌር፣ ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች አንዲቱ ማርያምን፣ ሸማይንና የኤሽትሞዓን አባት ይሽባን ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ፤ የሜሬድም ሚስት ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔዝራም ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌርና ያሎን ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ። ሜሬድም ቢትያ የተባለችውን የግብጽን ንጉሥ ልጅ አግብቶ ማርያም ተብላ የምትጠራውን ሴት ልጅና ሻማይና ዩሽባሕ ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዩሽባሕም ኤሽተሞዓ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ቈረቈረ፤ ሜሬድም ከይሁዳ ነገድ አንዲት ሴት አግብቶ የገዶርን ከተማ የቈረቈረውን ዬሬድን፥ የሶኮን ከተማ የቈረቈረውን ሔቤርንና፥ የዛኖሐን ከተማ የቈረቈረውን የቂቲኤልን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ፤ ዬቴርም ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደ። |
ንጉሡም ዳዊት ኦርናን፥ “አይደለም፥ ነገር ግን ለአንተ ያለውን ለእግዚአብሔር አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት በከንቱ አላቀርብምና በተገቢው ዋጋ እገዛዋለሁ” አለው።
ሚስቱ አይሂዳም የጌዶርን አባት ያሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህ ሞሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።
ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰማርያዋን፥ ሴልናንና መሰማሪያዋን፤ ኤስትሞዓንና መሰማሪያዋን ሰጡ።