“እግዚአብሔር ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ በዙሪያው ስለ ነበረ ጦርነት አባቴ ዳዊት ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ስም ቤት መሥራት እንዳልቻለ አንተ ታውቃለህ።
1 ዜና መዋዕል 28:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ግን፦ የሰልፍ ሰው ነህና፥ ብዙ ደምም አፍስሰሃልና ስሜ የሚጠራበትን ቤት አትሠራም ብሎኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ ‘ጦረኛ ሰው ስለ ሆንህና ደምም ስላፈሰስህ፣ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራም።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ግን፦ ‘የጦር አርበኛ ነህና፥ ደምም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም’ ብሎኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እኔ በጦርነት ብዙ ደም በማፍሰሴ ቤተ መቅደሱን እንድሠራለት እግዚአብሔር አልፈቀደልኝም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ግን ‘የሰልፍ ሰው ነህና፥ ደምም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም፤’ ብሎኛል። |
“እግዚአብሔር ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ በዙሪያው ስለ ነበረ ጦርነት አባቴ ዳዊት ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ስም ቤት መሥራት እንዳልቻለ አንተ ታውቃለህ።
“ሂድ፥ ለአገልጋዬ ለዳዊት ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጡ እኖርበት ዘንድ ቤትን የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤
ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፤ በፊቴም በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።