የሶርህያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ብላቴኖች ከኬብሮን ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፤ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ።
1 ዜና መዋዕል 27:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራተኛው ወር አራተኛው አለቃ የኢዮአብ ወንድም አሳሄል ነበረ፤ ከእርሱም በኋላ ልጁ ዝባድያና ወንድሞቹ ነበሩ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛው ወር፣ አራተኛው የበላይ አዛዥ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል ሲሆን፣ በእግሩ የተተካውም ልጁ ዝባድያ ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአራተኛው ወር አራተኛው አለቃ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ ከእርሱም በኋላ ልጁ ዝባድያ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ውስጥ ሀያ አራት ሺህ አባላት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአራተኛው ወር አራተኛው አለቃ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ ከእርሱም በኋላ ልጁ ዝባድያ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። |
የሶርህያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ብላቴኖች ከኬብሮን ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፤ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ።
የዳዊት ኀያላንም ስማቸው ይህ ነው። የኢዮአብ ወንድም አሣሄል በሠላሳው መካከል ነበረ፤ የቤተ ልሔም ሰው የአጎቱ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥
ደግሞም በጭፍሮቹ ዘንድ የነበሩት ኀያላን እነዚህ ናቸው፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፤