በሦስተኛው ወር ሦስተኛው የጭፍራ አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሽህ ጭፍራ ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ በናያስ ከሠላሳው መካከል ኀያል ሆኖ በሠላሳው ላይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ልጁ ዓሚዛባድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም በናያስ ከሠላሳዎቹ ይልቅ ኀያል ሲሆን፣ የሠላሳዎቹ የበላይ ነበረ፤ ልጁ ዓሚዛ ባድም የክፍሉ ሰራዊት አዛዥ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ በናያስ በሠላሳው መካከል ኃያል ሆኖ ሠላሳውን ያዝ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ልጁ ዓሚዛባድ ተሹሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ በናያስ በሠላሳው መካከል ኀያል ሆኖ በሠላሳው ላይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ልጁ ዓሚዛባድ ነበረ። |
በሦስተኛው ወር ሦስተኛው የጭፍራ አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሽህ ጭፍራ ነበረ።
በአራተኛው ወር አራተኛው አለቃ የኢዮአብ ወንድም አሳሄል ነበረ፤ ከእርሱም በኋላ ልጁ ዝባድያና ወንድሞቹ ነበሩ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።