1 ዜና መዋዕል 27:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዳን ወገንም ላይ የኢዮራም ልጅ ዓዛርኤል፤ እነዚህ የእስራኤል ነገዶች አለቆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዳን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል። እንግዲህ የእስራኤል ነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዳን ላይ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል አለቃ ነበረ፤ እነዚህ የእስራኤል ነገዶች አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዳን ላይ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል፤ እነዚህ የእስራኤል ነገዶች አለቆች ነበሩ። |
በገለዓድ ምድር ባለው በምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የዘብድያስ ልጅ ኢዮዳኢ፤ በብንያምም ልጆች ላይ የአበኔር ልጅ አሳሄል፤
ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉና የፍርድ አለቆችን፥ ንጉሡንም በየተራ የሚጠብቁትን አለቆቹን፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሡና በልጆቹ ሀብትና ንብረት ላይ፥ መባ ባለበት ላይ የተሾሙትን ጃንደረቦችንም፥ ኀያላኑንና ሰልፈኞቹን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።