1 ዜና መዋዕል 27:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌዊ ወገን ላይ የቀሙኤል ልጅ አሰብያ፤ በአሮን ወገን ላይ ሳዶቅ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌዊ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የቀሙኤል ልጅ ሐሸብያ፤ በአሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌዊ ላይ የቀሙኤል ልጅ ሐሸብያ አለቃ ነበረ፤ በአሮን ላይ ሳዶቅ አለቃ ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሌዊ ላይ የቀሙኤል ልጅ ሐሸብያ፤ በአሮን ላይ ሳዶቅ፤ |
እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ዐሥራ ስድስት አለቆች፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።
ከኬብሮናውያን ሐሳብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ፥ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር።
በእስራኤልም ነገዶች ላይ እነዚህ ነበሩ፦ በሮቤላውያን ላይ የዝክሪ ልጅ ኤልያዛር አለቃ ነበረ፤ በስምዖናውያን ልጅ የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ ነበረ፤