የይሁዳም ነገሥታት በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ አጠገብ በከተማው አቅራቢያ በነበረው በንጉሡ ጃንደረባ በናታን መኖሪያ አጠገብ ለፀሐይ የሰጡአቸውን ፈረሶች አቃጠለ፤ የፀሐይንም ሰረገሎች በእሳት አቃጠለ።
1 ዜና መዋዕል 26:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኦሳም በምዕራብ በኩል በሸለኬት በር ሦስት፥ በምሥራቅ በኩል በዐቀበቱ በር ከጥበቃ በላይ ጥበቃ በቀን ስድስት፥ በሰሜን በኩል አራት፥ በደቡብ በኩል አራት፥ በዕቃ ቤቱ በኩል ተቀባባዮች ሁለት ሁለት፥ በምዕራብ በኩል አራት በመተላለፊያውም መንገድ ተቀባባዮች ሁለት ሁለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምዕራቡ በኩል የሚገኘውን አደባባይ ደግሞ በመንገዱ ላይ አራት፣ በአደባባዩ ላይ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምዕራብ በኩል በምሶሶው አጠገብ ባለው መንገድ አራት፥ በምሶሶም አጠገብ ሁለት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምዕራብ በኩል መንገዱን ተጠግቶ በተሠራው አደባባይ አጠገብ አራት ዘብ ጠባቂዎች ሲመደቡ፥ ራሱን አደባባዩን የሚጠብቁ ሁለት ዘብ ጠባቂዎች ተመድበው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምዕራብ በኩል በፈርባር መንገድ ላይ አራት፥ በፈርባርም አጠገብ ሁለት ነበሩ። |
የይሁዳም ነገሥታት በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ አጠገብ በከተማው አቅራቢያ በነበረው በንጉሡ ጃንደረባ በናታን መኖሪያ አጠገብ ለፀሐይ የሰጡአቸውን ፈረሶች አቃጠለ፤ የፀሐይንም ሰረገሎች በእሳት አቃጠለ።
በምሥራቅ በኩል ለየዕለቱ ስድስት፥ በሰሜን በኩል ለየዕለቱ አራት፥ በደቡብ በኩል ለየዕለቱ አራት፥ ለዕቃ ቤትም ሁለት ሁለት ነበሩ።