ሕዝቅያስንም ጠሩ፤ የቤቱም አዛዥ የኬልቅዩ ልጅ ኤልያቄም ጸሓፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሓፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ወጡ።
1 ዜና መዋዕል 26:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለተኛውም ኬልቅያስ፥ ሦስተኛውም ጥበልያ፥ አራተኛውም ዘካርያስ ነበረ፤ የሖሳ ልጆችና ወንድሞች ሁሉ ዐሥራ ሦስት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለተኛው ኬልቅያስ፣ ሦስተኛው ጥበልያ፣ አራተኛው ዘካርያስ፤ የሖሳ ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶቹ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለተኛውም ኬልቅያስ፥ ሦስተኛው ጥበልያ፥ አራተኛው ዘካርያስ ነበሩ፤ የሖሳ ልጆችና ወንድሞች ሁሉ ዐሥራ ሦስት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሒልቂያ፥ ጠባልያና ዘካርያስ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ ከሖሳ ቤተሰብ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች የሆኑ በድምሩ ዐሥራ ሦስት አባላት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለተኛውም ኬልቅያስ፥ ሦስተኛው ጥበልያ፥ አራተኛው ዘካርያስ ነበረ፤ የሖሳ ልጆችና ወንድሞች ሁሉ ዐሥራ ሦስት ነበሩ። |
ሕዝቅያስንም ጠሩ፤ የቤቱም አዛዥ የኬልቅዩ ልጅ ኤልያቄም ጸሓፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሓፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ወጡ።
ከሜራሪም ልጆች ለነበረው ለሖሳ ፊተኛውን በር የሚጠብቁ ልጆች ነበሩት፤ አለቃውም ሰምሪ ነበረ፤ በኵር አልነበረም፤ አባቱ ግን አለቃ አደረገው፤
እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገለግሉ ዘንድ የበረኞች አለቆች በየሰሞናቸው የሚጠብቁ እነዚህ ነበሩ።