ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፤ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይሁዳም ተዋጊዎች ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ።
1 ዜና መዋዕል 21:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም የቈጠራቸውን የሕዝቡን ድምር ለዳዊት ሰጠ፤ ከእስራኤልም ሁሉ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተገኙ፤ ከይሁዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተገኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ሰዎች ቍጥር ለዳዊት አቀረበ፤ እነዚህም በመላው እስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺሕ ሲሆኑ፣ ሁሉም ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብም የቈጠራቸውን የሕዝቡን ድምር ለዳዊት ሰጠ፤ ከእስራኤልም ሁሉ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎችን አገኘ፤ ከይሁዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎችን አገኘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለውትድርና አገልግሎት ብቁ የሆኑትን ሰዎች ጠቅላላ ድምር ለዳዊት አስታወቀ፤ እነርሱም ከእስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሲሆኑ፥ ከይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም የቈጠራቸውን የሕዝቡን ድምር ለዳዊት ሰጠ፤ ከእስራኤልም ሁሉ አንድ ሚሊዮን ከመቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎችን አገኘ፤ ከይሁዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎችን አገኘ። |
ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፤ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይሁዳም ተዋጊዎች ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ።
ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብ ላይ አሸነፈ፤ ኢዮአብም ወጥቶ በእስራኤል ሁሉ ላይ ተዘዋወረ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም መጣ።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡ እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበዛ ዘንድ ተናግሮ ነበርና ዳዊት ከሃያ ዓመት በታች የነበሩትን አልቈጠረም።
የሶርህያ ልጅ ኢዮአብም መቍጠር ጀመረ፤ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህ ነገር በእስራኤል ላይ ቍጣ ሆነ፤ ቍጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት የታሪክ መጽሐፍ አልተጻፈም።