ዳዊትም ኢያቡሳውያንን አስቀድሞ የሚመታ ሰው አለቃና መኰንን ይሆናል አለ። የሶርህያም ልጅ ኢዮአብ አስቀድሞ ወጣና ወጋቸው፥ አለቃም ሆነ።
1 ዜና መዋዕል 19:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብንና የኀያላኑን ሠራዊት ሁሉ ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ይህን ሲሰማ ኢዮአብንና መላውን ተዋጊ ሰራዊት ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብንና የኃያላኑን ሠራዊት ሁሉ ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ስለዚህ ጉዳይ ሰምቶ ከመላው ሠራዊት ጋር ኢዮአብን በእነርሱ ላይ አዘመተ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብንና የኀያላኑን ሠራዊት ሁሉ ላከ። |
ዳዊትም ኢያቡሳውያንን አስቀድሞ የሚመታ ሰው አለቃና መኰንን ይሆናል አለ። የሶርህያም ልጅ ኢዮአብ አስቀድሞ ወጣና ወጋቸው፥ አለቃም ሆነ።
ሠላሳ ሁለትም ሺህ ሰረገሎችን የሞዓካን ንጉሥና ሕዝቡንም ቀጠሩ፤ መጥተውም በሜድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአሞንም ልጆች ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ወደ ሰልፍ መጡ።