1 ዜና መዋዕል 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ለአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩትን የወርቅ ማርዳዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም የአድርአዛር ጦር አለቆች ያነገቧቸውን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም የአድርአዛር ባርያዎች ይሸከሟቸው የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት የሀዳድዔዜር ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖች አንግበውት የነበረውን ከወርቅ የተሠራ ጋሻ ሁሉ ማርኮ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ለአድርአዛር ባሪያዎች የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ። |
ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮችን አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ያድነው ነበር።
ከሚጢብሐትና ከተመረጡት ከአድርአዛር ከተሞች ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚህም ሰሎሞን የናሱን ኩሬና ዓምዶች የናሱንም ዕቃ ሠራ።