ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፤ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው ይባል ዘንድ ስምህ ለዘለዓለም ጽኑና ታላቅ ይሁን፤ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን።
1 ዜና መዋዕል 17:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኬ ሆይ፥ ቤት እንድትሠራለት ለባሪያህ በጆሮው ገልጠሃልና ስለዚህ አገልጋይህ ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ ባለሟልነትን አገኘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አምላኬ ሆይ፤ ቤት እንደምትሠራለት ለባሪያህ ገልጸህለታል፤ ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት አገኘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላኬ ሆይ! ቤት እንደምትሠራለት ለባርያህ ገልጠህለታልና ስለዚህ ባርያህ ወደ አንተ ለመጸለይ በልቡ ደፈረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላኬ ሆይ፥ አንተ ለእኔ ለባሪያህ ቤትን እንደምትሠራልኝ ስለ ገለጥክልኝ ይህን ጸሎት ለማቅረብ ድፍረት አገኘሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላኬ ሆይ! ቤት እንድትሠራለት ለባሪያህ ገልጠሃልና ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ በልቡ ደፈረ። |
ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፤ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው ይባል ዘንድ ስምህ ለዘለዓለም ጽኑና ታላቅ ይሁን፤ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደርግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል፤ ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።