አምላክ ሆይ፥ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ ስለ አገልጋይህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ። አቤቱ፥ አምላክ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ።
1 ዜና መዋዕል 17:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ባሪያህን ታውቀዋለህና ለባሪያህ ስለ ተደረገው ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚለው ምንድን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ባሪያህን ስላከበርኸው፣ ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? ባሪያህን አንተ ታውቀዋለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ባርያህን ታውቀዋለህና ለባርያህ ስለተደረገው ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚለው ምን ነገር አለው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ለአንተ ከዚህ በላይ ምን መናገር እችላለሁ? አንተ እኔን ታውቀኛለህ፤ ይሁን እንጂ ለእኔ ክብር ሰጥተኸኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ባሪያህን ታውቀዋለህና ለባሪያህ ስለ ተደረገው ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚለው ምንድር ነው? |
አምላክ ሆይ፥ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ ስለ አገልጋይህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ። አቤቱ፥ አምላክ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ።
ሦስተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ ጴጥሮስም ሦስት ጊዜ ትወደኛለህን? ስላለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እኔም እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “እንኪያስ ግልገሎችን ጠብቅ” አለው።
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፥ “ፊቱን፥ የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።
ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት፤ ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።