1 ዜና መዋዕል 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ እግዚአብሔርም ያደረገውን ተአምራቱን ሁሉ ተናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተቀኙለት፤ ዘምሩለት፤ ድንቅ ሥራዎቹንም ሁሉ ተናገሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ ያደረገውን አስደናቂ ነገር ሁሉ ተናገሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተቀኙለት፤ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ። |
የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት የዘመርዋት መዝሙር ይህች ናት፦ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ ስሙንም ጥሩ፤ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ።
ስሙ ለዘለዓለም ቡሩክ ነው፥ ከፀሓይም አስቀድሞ ስሙ ነበረ፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ፥ ሕዝቡ ሁሉ ያመሰግኑታል።
የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፣ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።
በጥበብ ሁሉ እንድትበለጽጉ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ዘንድ ይጽና፤ በመንፈስም ራሳችሁን አስተምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝሙርንና ምስጋናን፥ የቅድስና ማሕሌትንም በልባችሁ በጸጋ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።