“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ ለስምህ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!
1 ዜና መዋዕል 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ዳዊት፥ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ?” ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በዚያ ዕለት እግዚአብሔርን ስለ ፈራ፣ “ታዲያ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት ማምጣት እችላለሁ?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ዳዊት፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ?” ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዳዊት እግዚአብሔርን እጅግ ስለ ፈራ “እንግዲህ ይህን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቴ እንዴት መውሰድ እችላለሁ?” አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ዳዊት “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ?” ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ። |
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ ለስምህ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!
ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ጌት ሰው ወደ አቢዳራ ቤት አሳለፋት እንጂ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ አላመጣትም።
ዳዊት ግን ከእግዚአብሔር መልአክ ሰይፍ የተነሣ ስለ ፈራ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደዚያ ይሄድ ዘንድ አልቻለም።
እኔም፥ “ከንፈሮች የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዐይኖች የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!” አልሁ።
የቤትሳሚስም ሰዎች፥ “በዚህ በቅዱሱ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ማለፍ ማን ይችላል? የእግዚአብሔር ታቦት ከእኛ ወጥታ ወደ ማን ትሄዳለች?” አሉ።