1 ዜና መዋዕል 12:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንፍታሌምም አለቆች አንድ ሺህ ነበሩ፥ ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የሚይዙ ሠላሳ ሰባት ሺህ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንፍታሌም ሰዎች አንድ ሺሕ የጦር አለቆች፤ ከእነርሱም ጋራ ጋሻና ጦር የያዙ ሠላሳ ሰባት ሺሕ ሰዎች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንፍታሌምም አለቆች አንድ ሺህ ነበሩ፥ ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የታጠቁ ሠላሳ ሰባት ሺህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንፍታሌምም አለቆች አንድ ሺህ ነበሩ፤ ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የሚይዙ ሠላሳ ሰባት ሺህ ነበሩ። |
በጭፍራውም ውስጥ ዳዊትን ለመርዳት የወጡ የተዘጋጁ፥ መሣሪያም ሁሉ የያዙ የዛብሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ፤ ከእነርሱ አንድስ እንኳ ደካማ አልነበረም።