1 ዜና መዋዕል 12:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ እግዚአብሔርም ቃል የሳኦልን መንግሥት ወደ እርሱ ይመልሱ ዘንድ በኬብሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመጡት የሠራዊቱ አለቆች ቍጥር ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ለዳዊት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት፣ የሳኦልን መንግሥት አንሥተው ለርሱ ለመስጠት ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ ኬብሮን የመጡት ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ጌታም ቃል የሳኦልን መንግሥት ወደ እርሱ ለመመለስ በኬብሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመጡት የሠራዊቱ አለቆች ቍጥር ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በኬብሮን ሳለ ብዙ የሠለጠኑ ወታደሮች ወደ እርሱ ሠራዊት ገቡ፤ እግዚአብሔር በሰጠውም የተስፋ ቃል መሠረት በሳኦል እግር ተተክቶ እንዲነግሥ ብዙ ርዳታ አደረጉለት፤ ቊጥራቸውም እንደሚከተለው ነበር፦ ከይሁዳ ነገድ፦ ጋሻና ጦር በሚገባ የታጠቁ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ወታደሮች፥ ከስምዖን ነገድ፦ በሚገባ የሠለጠኑ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ወታደሮች፥ ከሌዊ ነገድ፦ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች፤ የአሮን ዘሮች የሆኑት የዮዳሄ ተከታዮች ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ታዋቂ ጦረኛ ከሆነው ከጻዶቅ ዘመዶች፦ ኻያ ሁለት የጦር አዛዦች፥ የሳኦል ወገን ከሆነው ከብንያም ነገድ፦ ሦስት ሺህ ሰዎች፤ ይሁን እንጂ ከብንያም ነገድ አብዛኛው ሕዝብ ለሳኦል ያላቸውን ታማኝነት እንደ ቀጠሉ ነበሩ። ከኤፍሬም ነገድ፦ ኻያ ሺህ ስምንት መቶ ሰዎች ሲሆኑ፥ ሁሉም በየጐሣቸው ዝነኞች የሆኑ ጀግኖች ነበሩ። በምዕራብ በኩል ካለው ከምናሴ ነገድ፦ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ሲሆኑ፥ እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በተለይ የተመረጡ ናቸው። ከይሳኮር ነገድ፦ ሁለት መቶ መሪዎች ሲሆኑ፥ በእነርሱ አመራር ሥር ያሉትንም ያጠቃልላል፤ እነዚህ መሪዎች እስራኤል ምን ማድረግና መቼ ማድረግ እንደሚገባት የሚያውቁ ናቸው። ከዛብሎን ነገድ፦ እምነት የሚጣልባቸው ለጦርነት ዝግጁዎች የሆኑ በማንኛውም መሣሪያ መጠቀም የሚችሉ ኀምሳ ሺህ ወታደሮች፤ ከንፍታሌም ነገድ፦ አንድ ሺህ የጦር መሪዎችና ጋሻና ጦር ያነገቡ ሠላሳ ሰባት ሺህ ወታደሮች ነበሩ። ከዳን ነገድ፦ ኻያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ የሠለጠኑ ወታደሮች ነበሩ። ከአሴር ነገድ፦ አርባ ሺህ ለጦርነት የተዘጋጁ ወታደሮች ነበሩ። ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ካሉት ከሮቤል፥ ከጋድና ከምናሴ ነገዶች፦ በማንኛውም ዐይነት መሣሪያ የመጠቀም ችሎታ ያላቸው አንድ መቶ ኻያ ሺህ ወታደሮች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ እግዚአብሔርም ቃል የሳኦልን መንግሥት ወደ እርሱ ይመልሱ ዘንድ በኬብሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመጡት የሠራዊቱ አለቆች ቍጥር ይህ ነው። |
እግዚአብሔርም ስለ ዳዊት፦ በባሪያዬ በዳዊት እጅ ሕዝቤን እስራኤልን ክፍልስጥኤማውያን እጅና ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ አድናለሁ ብሎ ተናግሮአልና እንግዲህ አሁን አድርጉ´ ብሎ ነገራቸው።
ነቢዩ ሳሙኤልም መለሰለት፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ ዘንድ አልሰማውም፥ ስለዚህ ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳለፈው።
ለዳዊትም የነበሩት ኀያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያነግሡት ዘንድ ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ አጸኑት።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? የዘይቱን ቀንድ ሞልተህ ና፤ በልጆቹ መካከል ለእኔ ንጉሥ አዘጋጅቼአለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ” አለው።