1 ዜና መዋዕል 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሣሪያውንም በአምላኮቻቸው ቤት ውስጥ አኖሩ፤ ራሱንም በዳጎን ቤት ውስጥ አኖሩት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጦር መሣሪያውን በአማልክታቸው ቤተ ጣዖት አስቀመጡት፤ ራሱንም በዳጎን ቤተ ጣዖት ውስጥ አንጠለጠሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሣሪያውንም በአምላኮቻቸው ቤት ውስጥ አኖሩ፤ ራሱንም በዳጎን ቤት ውስጥ ቸነከሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦልን የጦር መሣሪያዎች በአማልክታቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖሩ፤ ራሱንም ዳጎን ተብሎ በሚጠራው አምላካቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ሰቀሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሣሪያውንም በአምላኮቻቸው ቤት ውስጥ አኖሩ፤ ራሱንም በዳጎን ቤት ውስጥ ቸነከሩት። |
ሳኦልንም ገፈፉት፥ ራሱንም ቈርጠው መሣሪያውንም አንሥተው ለጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራች ይወስዱ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ሀገር ዙሪያ ሰደዱ።