ሶፎንያስ 3:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ከተማዪቱን፣ ‘በርግጥ ትፈሪኛለሽ፤ ዕርምትም ትቀበያለሽ’ አልኋት፤ ስለዚህ መኖሪያዋ አይጠፋም፤ ቅጣቴም ሁሉ በርሷ ላይ አይደርስም። እነርሱ ግን በሚያደርጉት ሁሉ፣ ክፋትንም በመፈጸም እየተጉ ሄዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም አልኩ “በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፥ እርማትንም ትቀበያለሽ፤ መኖሪያዋ አይጠፋም፥ ያቀድኩትም አይደርስም።” እነርሱ ግን በማለዳ ተነሥተው ድርጊታቸውን ሁሉ አረከሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ይህን ሁሉ በማድረጌ ‘ሕዝቤ ያከብረኛል፤ ተግሣጼንም ይቀበላል፤ የደረሰበትንም ተግሣጽ ሁሉ አይረሳም’ ብዬ ነበር፤ ሕዝቤ ግን እየባሰበት ሄደ፤ በክፉ ሥራውም ረከሰ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም- ይፈሩኛል፥ ተግሣጽንም ይቀበላሉ፣ ካዘዝኋትም ሁሉ ከዓይንዋ ምንም አይጠፋም ብዬ ነበር፣ እነርሱ ግን በማለዳ ተነሥተው ድርጊታቸውን ሁሉ አረከሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ ይፈሩኛል፥ ተግሣጽንም ይቀበላሉ፥ ካዘዝኋትም ሁሉ ከዓይንዋ ምንም አይጠፋም ብዬ ነበር፥ እነርሱ ግን በማለዳ ተነሥተው ድርጊታቸውን ሁሉ አረከሱ። |
ስለዚህ እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሰራዊት አዛዦች አመጣባቸው፤ እነርሱም በምናሴ አፍንጫ መንጠቆ አገቡበት፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም ወደ ባቢሎን ወሰዱት።
እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “እንግዲህ ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤ እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ለዘላለም ትቀመጣላችሁ።
ምናልባትም የይሁዳ ሕዝብ ላመጣባቸው ያሰብሁትን ጥፋት ሁሉ ሲሰሙ፣ እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ክፋታቸውንና ኀጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”
ኤርምያስም ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ብትሰጥ፣ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ አትቃጠልም፤ አንተና ቤተ ሰብህም በሕይወት ትኖራላችሁ።
እኔ በጥንቃቄ አደመጥኋቸው፤ ትክክለኛ የሆነውን ግን አይናገሩም። ማንም ስለ ክፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤ “ምን አድርጌአለሁ?” ይላል። ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ፈረስ፣ እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይሄዳል።
አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።