ሩት 4:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የመቤዠት ቅድሚያ ያለውን ቅርብ የሥጋ ዘመድ እንዲህ አለው፤ “ከሞዓብ የተመለሰችው ኑኃሚን፣ የወንድማችንን የአሊሜሌክን ጢንጦ መሬት ልትሸጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦዔዝም የቅርብ ዘመዱን፦ “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ናዖሚ የወንድማችንን ኤሊሜሌክን መሬት መሸጥ ትፈልጋልች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቦዔዝም የቅርብ ዘመድ የሆነውን ሰው እንዲህ አለው፦ “እነሆ ናዖሚ ከሞአብ አገር ተመልሳ መጥታለች፤ የዘመዳችንን የአቤሜሌክንም መሬት መሸጥ ትፈልጋለች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቦዔዝም የቅርብ ዘመዱን፦ ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቤሜሌክን ጢንጦ ትሸጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቦዔዝም የቅርብ ዘመዱን “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቤሜሌክን መሬት ትሸጣለች። |
የሰውየው ስም አሊሜሌክ፣ የሚስቱ ኑኃሚን፣ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበር። እነርሱም የይሁዳ ቤተ ልሔም ኤፍራታውያን ሲሆኑ፣ ወደ ሞዓብ አገር ሄደው በዚያ ኖሩ።