የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩና ሕዝቤን በበኣል እንዲምል እንዳስተማሩት ሁሉ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው በስሜ ቢምሉ፣ በዚያ ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ፤
ሩት 3:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ ዕደሪ፤ ሲነጋም ሰውየው ሊቤዥሽ ከፈለገ፣ መልካም ነው፤ ይቤዥሽ፤ የማይፈልግ ከሆነ ግን በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ፤ እኔ እቤዥሻለሁ፤ እስኪነጋም ድረስ እዚሁ ተኚ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬ ሌሊት እደሪ፥ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድ መልካም ነው፥ ዋርሳ ይሁን፥ ዋርሳ ሊሆን ባይወድ ግን፥ ሕያው ጌታን እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፥ እስኪ ነጋ ድረስ ተኚ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስኪነጋ እዚሁ ቈዪ! ሲነጋም ያ ሰው ስለ አንቺ ኀላፊነትን የሚወስድ መሆኑን ወይም አለመሆኑን እጠይቀዋለሁ፤ እርሱ ኀላፊነትን የሚወስድ ከሆነ መልካም ነው፤ የማይወስድ ከሆነ ግን ስለ አንቺ ኀላፊነትን እኔ እንደምወስድ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ አሁንም ተኚ፤ እስኪነጋም ድረስ እዚሁ ቈዪ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬ ሌሊት እደሪ፣ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድድ መልካም ነው፥ ዋርሳ ይሁን፣ ዋርሳ ሊሆን ባይወድድ ግን፥ ሕያው እግዚአብሔርን እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፣ እስኪነጋ ድረስ ተኚ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬ ሌሊት እደሪ፤ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድድ መልካም ነው፤ ዋርሳ ይሁን፤ ዋርሳ ሊሆን ባይወድድ ግን፥ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፤ እስኪነጋ ድረስ ተኚ።” |
የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩና ሕዝቤን በበኣል እንዲምል እንዳስተማሩት ሁሉ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው በስሜ ቢምሉ፣ በዚያ ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ፤
ጌዴዎንም፣ “እነርሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ናቸው፤ ባትገድሏቸው ኖሮ እኔም እንደማልገድላችሁ በሕያው እግዚአብሔር ስም አረጋግጥላችሁ ነበር።” ብሎ መለሰላቸው።
ኑኃሚንም ምራቷን፣ “በጎነቱን ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ማድረጉን ያልተወ እግዚአብሔር ይባርከው” አለቻት፤ ቀጥላም፣ “ሰውየው እኮ የሥጋ ዘመዳችን ነው፤ የመቤዠት ግዴታ ካለባቸው ዘመዶቻችን አንዱ እርሱ ነው” አለቻት።
ከዚያም ቦዔዝ፣ “እንግዲህ መሬቱን ከኑኃሚንና ከሞዓባዊቷ ከሩት ላይ በምትገዛበት ዕለት፣ የሟቹን ስም በርስቱ ለማስጠራት ሚስቱንም ዐብረህ መውሰድ አለብህ” አለው።
ያም ቅርብ የሥጋ ዘመድ፣ “እንዲህ ከሆነማ የራሴን ርስት አደጋ ላይ ልጥል ስለምችል፣ እኔ ልቤዠው አልችልም፤ አንተው ራስህ ተቤዠው” አለው።