የነቢያት ማኅበር ወገን ከሆነው የአንደኛው ሚስት፣ “አገልጋይህ ባሌ ሞቷል፤ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበር አንተ ታውቃለህ፤ አሁን ግን ባለዕዳ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ባሪያ አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቷል” ስትል ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
ሩት 1:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኑኃሚን ባል አሊሜሌክ ሞተ፤ ኑኃሚንም ከሁለት ልጆቿ ጋራ ብቻዋን ቀረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናዖሚም ባል ኤሊሜሌክ ሞተ፥ እርሷም ከሁለቱ ልጆችዋ ጋር ቀረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የናዖሚ ባል ኤቤሜሌክ ሞተ፤ ናዖሚም ከሁለቱ ልጆችዋ ጋር ብቻዋን ቀረች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ ሞተ፣ እርስዋና ሁለቱ ልጆችዋ ቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ ሞተ፤ እርስዋና ሁለቱ ልጆችዋ ቀሩ። |
የነቢያት ማኅበር ወገን ከሆነው የአንደኛው ሚስት፣ “አገልጋይህ ባሌ ሞቷል፤ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበር አንተ ታውቃለህ፤ አሁን ግን ባለዕዳ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ባሪያ አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቷል” ስትል ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
የሰውየው ስም አሊሜሌክ፣ የሚስቱ ኑኃሚን፣ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበር። እነርሱም የይሁዳ ቤተ ልሔም ኤፍራታውያን ሲሆኑ፣ ወደ ሞዓብ አገር ሄደው በዚያ ኖሩ።