ራእይ 10:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደሚያገሣ አንበሳም ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ የሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፆች ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓዶች በየድምፃቸው ተናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያገሣ የአንበሳን ድምፅ በመሰለ ታላቅ ድምፅም ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፃቸውን አሰሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል የሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣ ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበት፣ ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣ በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።
“እንግዲህ ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ተናገርባቸው፤ እንዲህም በላቸው፣ “ ‘እግዚአብሔር ከላይ ይጮኻል፤ ከቅዱስ ማደሪያው ነጐድጓዳማ ድምፁን ያሰማል፤ በራሱ ምድር ላይ እጅግ ይጮኻል፤ እንደ ወይን ጨማቂዎች፣ በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይም ያስገመግማል፤
እግዚአብሔር ከጽዮን ጮኾ ይናገራል፤ ከኢየሩሳሌም ያንጐደጕዳል፤ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፣ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።
እርሱም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ከጽዮን ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፤ ከኢየሩሳሌምም ያንጐደጕዳል፤ የእረኞች ማሰማሪያዎች ደርቀዋል፤ የቀርሜሎስም ዐናት ጠውልጓል።”
ከሰማይ እንደ ብዙ ውሃ ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የሰማሁት ድምፅ በገና ደርዳሪዎች እንደሚደረድሩት ዐይነት ነበረ።
ሌላም ታላቅና አስደናቂ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የመጨረሻዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት አየሁ፤ የመጨረሻ የተባሉትም የእግዚአብሔር ቍጣ የሚፈጸመው በእነርሱ በመሆኑ ነው።
ከዚያም ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖረው አምላክ ቍጣ የተሞሉትን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።