መዝሙር 99:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤ በቅዱስ ተራራውም ላይ ስገዱ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፥ ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና፥ እርሱን አክብሩት፤ በተቀደሰው ተራራም ላይ ስገዱለት፥ |
ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋራ እሆናለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቀድሞው ያለህ አይደለህምን? የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ አትሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርድ ሾመኸዋል፤ ዐለት ሆይ፤ ይቀጣ ዘንድ ሥልጣን ሰጥተኸዋል።
“በፊላድልፍያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው፣ የዳዊትንም መክፈቻ በእጁ የያዘው እንዲህ ይላል፤ እርሱ የከፈተውን ማንም ሊዘጋው አይችልም፤ የዘጋውንም ማንም ሊከፍተው አይችልም።
አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች ነበሯቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸው በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ፤ ቀንና ሌሊትም፦ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፤ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ” ማለትን አያቋርጡም።