መዝሙር 90:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ሆይ፤ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት። አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! በዘመናት ሁሉ አንተ መጠጊያችን ነህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልዑል ረድኤት የሚያድር፥ በሰማይ አምላክ ጥላ ውስጥ የሚቀመጥ፥ |
እርሱም መቅደስ ይሆናል፤ ለሁለቱ የእስራኤል ቤት ግን የሚያደናቅፍ ድንጋይ፣ የሚጥልም ዐለት ይሆንባቸዋል፤ ለኢየሩሳሌም ሕዝብም ወጥመድና አሽክላ ይሆናል።
“ስለዚህ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በአሕዛብ መካከል ብሰድዳቸውም፤ በአገሮች መካከል ብበታትናቸውም፣ በሄዱባቸው አገሮች ሁሉ ለጥቂት ጊዜ መቅደስ ሆኛቸዋለሁ።’
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቀድሞው ያለህ አይደለህምን? የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ አትሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርድ ሾመኸዋል፤ ዐለት ሆይ፤ ይቀጣ ዘንድ ሥልጣን ሰጥተኸዋል።
የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን ተከታተል።
ስለዚህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ በፍቅሩም እናምናለን። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል።