“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንድሠራለት አዝዞኛል።
መዝሙር 85:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝብህን በደል ይቅር አልህ፤ ኀጢአታቸውንም ሁሉ ሸፈንህ። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ምድርህን በመልካም ጎበኘህ፥ የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕዝብህን በደል ይቅር አልክ፤ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ደመሰስክ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ የዋህ ነኝና ነፍሴን ጠብቃት፤ አምላኬ ሆይ፥ አንተን የታመነውን ባሪያህን አድነው። |
“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንድሠራለት አዝዞኛል።
በእነዚያ ጊዜያት፣ በዚያ ዘመን፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ አንዳችም አይገኝም፤ የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፤ ከቶም የለም፤ እንዲተርፉ ያደረግኋቸውን ቅሬታዎች እምራለሁና።
የርስቱን ትሩፍ ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? ለዘላለም አትቈጣም፤ ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል።
ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ይቅር እንዳልሃቸው ሁሉ እንደ ፍቅርህ ታላቅነት መጠን እባክህ አሁንም የዚህን ሕዝብ ኀጢአት ይቅር በል።”
እናንተም በበደላችሁና የሥጋችሁን ኀጢአታዊ ባሕርይ ባለመገረዝ ሙታን ነበራችሁ፣ እግዚአብሔር ግን ከክርስቶስ ጋራ ሕያዋን አደረጋችሁ፤ በደላችንንም ሁሉ ይቅር አለን፤